በኢትዮጵያ አዲስ ደንበኞች የሚያመጣ የSEO አገልግሎት

ዌብሳይትዎ ኢንተርኔት ላይ ተውጦ አልታይ ብሏል? በፍለጋ በኩል ብዙ ደንበኛ አግኝተው ንግድዎን ማሳደግ ይፈልጋሉ? WubSites አዲስ አበባ ውስጥ የሚታመኑበት የSEO (በGoogle ፍለጋ ላይ ቀድሞ መገኘት) አጋርዎ ነው።

ከWubSites ጋር በሰራው ስራ ውጤት የተደሰተ ኢትዮጵያዊ ሞዴል።
የWubSites ቡድን ለአንድ የኢትዮጵያ አነስተኛ ንግድ የኦንላይን ሽያጭ ዌብሳይት በጋራ ሲሰራ

ለSEO WubSitesን ለምን ይመርጣሉ?

የአገር ውስጥ እውቀት፡ የኢትዮጵያን ገበያ ፈተናና ዕድል እናውቃለን። ንግድዎ በአካባቢ ፍለጋ ላይ ከፍ ብሎ እንዲታይ አሰራራችንን ከዚሁ ጋር እናስማማለን።

የተረጋገጠ ውጤት፡ ስራችን ይመሰክራል። አዲስ አበባ ውስጥ ብዙ ንግዶች በፍለጋ ላይ ከፊት እንዲታዩና ከፍለጋ የሚመጣ ጎብኚያቸው እንዲጨምር ረድተናል።

ሁሉን ያቀፈ አሰራር፡ በቁልፍ ቃልና በሊንክ ብቻ አንወሰንም። የዌብሳይትዎን ቴክኒካል ክፍል፣ ይዘቱን እና ለተጠቃሚ ያለውን ምቾት ሁሉንም እናሻሽላለን።

ግልጽ ግንኙነት፡ በእያንዳንዱ ደረጃ እናሳውቅዎታለን፤ የSEO ስራዎ የደረሰበትን በየጊዜው በሪፖርት እናቀርባለን።

የSEO አገልግሎቶቻችን

የቁልፍ ቃል ጥናት፡ ለንግድዎና ለደንበኞችዎ በጣም የሚስማሙትን የፍለጋ ቃላት እንለያለን።

በዌብሳይቱ ላይ የሚሰራ SEO፡ የዌብሳይትዎን ይዘት፣ ሜታ ታጎች እና ርዕሶች አስተካክለን በፍለጋ ላይ የተሻለ ደረጃ እንዲያገኝ እናደርጋለን።

ቴክኒካል SEO፡ ዌብሳይትዎ ቴክኒካል ችግር እንዳይኖርበትና Google በቀላሉ እንዲያነበው እናደርጋለን።

ከዌብሳይቱ ውጭ የሚሰራ SEO፡ ጥራት ካላቸው ድረ-ገጾች ወደ ዌብሳይትዎ የሚወስዱ ሊንኮች እናስገኛለን፤ ዌብሳይትዎ Google ዘንድ የበለጠ እንዲታመን የሚያደርጉ ሌሎች ስራዎችንም እንሰራለን።

የአካባቢ SEO፡ ከአካባቢዎ ብዙ ደንበኛ እንዲመጣ Google My Business ገጽዎንና በኦንላይን የንግድ ማውጫዎች ላይ ያለውን የድርጅትዎን መረጃ እናስተካክላለን።

የSEO ኦዲት፡ ዌብሳይትዎን በሙሉ መርምረን መሻሻል ያለበትን እንለያለን፤ ለእርስዎ የሚስማማ የSEO ዕቅድም እናዘጋጃለን።

የWubSites ግራፊክ ዲዛይነር ለኢትዮጵያ አስመጪና ላኪ ድርጅት ልዩ ሎጎ ሲሰራ

የSEO አገልግሎታችን ምን ያካትታል

SEO ማለት ሰዎች እርስዎ የሚሸጡትን ነገር Google ላይ ሲፈልጉ ዌብሳይትዎ እንዲታይ የሚያደርግ ስራ ነው። በኦዲት (ምርመራ) እንጀምራለን፤ ከዚያ የተገኙትን ችግሮች አንድ በአንድ እናስተካክላለን፡

  • የቁልፍ ቃል ጥናት፡ ደንበኞችዎ Google ላይ በትክክል የሚጽፏቸውን ቃላት ማግኘት።
  • በገጾቹ ላይ የሚሰራ ስራ፡ የገጽ ርዕሶች፣ ንዑስ ርዕሶች፣ ጽሑፍ እና በገጾችዎ መካከል ያሉ ሊንኮች።
  • ቴክኒካል ማስተካከያ፡ ፍጥነት፣ በስልክ ላይ ያለው አቀማመጥ እና Google ዌብሳይቱን እንዳያነብ የሚከለክል ማንኛውም ነገር።
  • የአካባቢ SEO፡ Google Business Profile ገጽዎ እና ኦንላይን የንግድ ማውጫዎች፤ በአካባቢዎ ለሚደረጉ ፍለጋዎች ንግድዎ እንዲታይ።
  • ከዌብሳይቱ ውጭ የሚሰራ ስራ፡ ከሌሎች ታማኝ ድረ-ገጾች የሚመጡ ሊንኮችና የድርጅትዎ ስም መጠቀሱ።

ስራው እንዴት ይሄዳል

  1. ነፃ ምክክር። ዌብሳይትዎን እናያለን፤ እርስዎም የትኞቹን ደንበኞች በብዛት እንደሚፈልጉ ይነግሩናል።
  2. ኦዲት። ዌብሳይቱን መርምረን ወደ ኋላ የሚጎትቱትን ነገሮች ከዋናው ጀምረን እንዘረዝራለን።
  3. ዕቅድና የዋጋ ግምት። የምንሰራውን ያያሉ፣ ግልጽ ዋጋም አስቀድመው ያገኛሉ።
  4. ማስተካከያና ይዘት። መጀመሪያ ቴክኒካል ችግሮቹን እናስተካክላለን፤ ከዚያ ገጾችን እናሻሽላለን ወይም እንጨምራለን።
  5. ሪፖርት። ምን እንደተሰራ፣ ደረጃዎና የጎብኚዎ ቁጥር እንዴት እየተቀየረ እንደሆነ እናሳውቅዎታለን።

ለማን ነው

SEO ደንበኞቻቸው ከመግዛታቸው በፊት ኢንተርኔት ላይ ለሚፈልጉ ንግዶች ይጠቅማል፡ ሆቴሎችና አስጎብኚ ድርጅቶች፣ ክሊኒኮች፣ ትምህርት ቤቶች፣ አስመጪዎች፣ አምራቾችና ላኪዎች፣ የሙያ አገልግሎት ድርጅቶች እና የኦንላይን ሱቆች።

SEO በደንብ የሚሰራው ዌብሳይቱ ራሱ በደንብ ሲሰራ ነው። የእርስዎ ቀርፋፋ ከሆነ ወይም በስልክ ለመጠቀም የሚያስቸግር ከሆነ መጀመሪያ እሱን እንዲያስተካክሉ ልንመክር እንችላለን። ቀለል ያለ መግቢያ ከፈለጉ SEO ለአዲስ አበባ አነስተኛ ንግዶች የሚለውን ይመልከቱ።

ከእርስዎ የምንፈልገው

  • ለውጦቹን እንድናደርግ ወደ ዌብሳይትዎ የመግባት ፈቃድ (አክሰስ)።
  • Google Search Console፣ Google Analytics እና Google Business Profile ካለዎት ወደ እነሱ የመግባት ፈቃድ (አክሰስ)።
  • የዋና ዋና ምርቶችዎ ወይም አገልግሎቶችዎ እና የሚያገለግሏቸው አካባቢዎች አጭር ዝርዝር።
  • አዲስ የገጽ ጽሑፍ አንብቦ የሚያጸድቅ ሰው።

ስለ SEO የሚነሱ ጥያቄዎች

SEO ውጤት ለማሳየት ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?

ብዙ ጊዜ ጥቂት ወራት። ቴክኒካል ማስተካከያዎች ቶሎ ሊረዱ ይችላሉ፤ ውድድር ባለባቸው ፍለጋዎች ላይ ግን ደረጃው ቀስ በቀስ ነው የሚመጣው፣ በተወዳዳሪዎችዎ ጥንካሬም ይወሰናል።

ዌብሳይቴ Google ላይ አንደኛ እንደሚሆን ዋስትና ትሰጣላችሁ?

አንሰጥም፤ በታማኝነት ሊሰጥ የሚችልም የለም፣ ደረጃውን የሚወስነው Google ነውና። እኛ ቃል የምንገባው ስራውን ነው፡ በደንብ የሚሰራ ዌብሳይት፣ ጠቃሚ ገጾች እና ስለ ሂደቱ ግልጽ ሪፖርት።

የአካባቢ SEO ምንድን ነው?

በአቅራቢያዎ ያሉ ሰዎች ንግድዎን እንዲያገኙ የሚያደርገው የSEO ክፍል ነው፤ ለምሳሌ ቦሌ ውስጥ የጥርስ ሐኪም ለሚፈልግ ሰው። ለዚህ የሚያስፈልጉት፡ Google Business Profile ገጽዎ፣ የድርጅትዎ ስም፣ አድራሻና ስልክ ቁጥር ኢንተርኔት ላይ በሁሉም ቦታ አንድ ዓይነት መሆኑ እና የደንበኞች አስተያየት (review) ናቸው።

SEO ንግዴ እንደ ChatGPT ባሉ የAI መልሶች ላይ እንዲታይ ይረዳል?

በአብዛኛው አዎ። እንደ ChatGPT ያሉ AI መሳሪያዎችም Google የሚያያቸውን ነገሮች ነው የሚያዩት፡ ግልጽ ገጾች፣ በሁሉም ቦታ አንድ ዓይነት የሆነ የንግድ መረጃ እና በሌሎች ድረ-ገጾች ላይ መጠቀስ። ይህንን ChatGPT፣ Gemini እና Google AI ንግድዎን ለሰዎች እንዲጠቁሙ ምን ማድረግ አለብዎት? በሚለው ጽሑፋችን አብራርተናል።

Facebook እና Telegram ላይ እለጥፋለሁ። SEO ያስፈልገኛል?

ሁለቱ ስራቸው የተለያየ ነው። ሶሻል ሚዲያ ሰዎችን ስክሮል ሲያደርጉ ያገኛቸዋል። ፍለጋ ደግሞ እርስዎ የሚሸጡትን ነገር በሚፈልጉበት ሰዓት ያገኛቸዋል። ሁለቱ እንዴት አብረው እንደሚሰሩ ለኢትዮጵያ አነስተኛና መካከለኛ ንግዶች የዲጂታል ማርኬቲንግ ስትራቴጂ የሚለው መመሪያችን ያሳያል።

ዌብሳይትዎን ወደ ኋላ የሚጎትተው ምን እንደሆነ ማወቅ ይፈልጋሉ? የዋጋ ግምት መጠየቂያ ፎርሙን ሞልተው ስለ ንግድዎ ይንገሩን። ግልጽ ዋጋ አስቀድመው ያገኛሉ።

ጥያቄዎን ይጻፉልን
ይህን ፎርም ይሙሉ፤ የዋጋ ግምት በፍጥነት እንልክልዎታለን።

Google Analytics የGoogle የዌብሳይት ትንተና አገልግሎት ነው። Google የሚሰበሰበውን መረጃ የዚህን ዌብሳይት አጠቃቀም ለመከታተል፣ ስለ እንቅስቃሴው ሪፖርት ለማዘጋጀት እና ለሌሎች የGoogle አገልግሎቶች ለማጋራት ይጠቀምበታል።

Google የተሰበሰበውን መረጃ በራሱ የማስታወቂያ ኔትወርክ ላይ የሚያሳያቸውን ማስታወቂያዎች ለእርስዎ እንዲስማሙ ለማድረግ ሊጠቀምበት ይችላል።

የሚሰበሰብ የግል መረጃ፡ ኩኪ እና የአጠቃቀም መረጃ። መረጃው የሚስተናገድበት ቦታ፡ አሜሪካ። የGoogleን የግላዊነት ፖሊሲ እዚህ ያገኛሉ።

የግላዊነት ፖሊሲ