ሎጎና ብራንዲንግ ዲዛይን በአዲስ አበባ

ብራንዲንግ ሎጎ ብቻ አይደለም። የድርጅትዎ ገጽታ ነው፤ ሰዎች ስለ ድርጅትዎ መጀመሪያ የሚያዩት ነገር። ምስል ብዙ እንደሚናገር WubSites ያውቃል። ዲዛይነሮቻችን ከእርስዎ ጋር በቅርበት እየሰሩ፣ የድርጅትዎን ማንነት የሚያሳይና የማይረሳ ብራንድ ይሰሩልዎታል።

የWubSites ግራፊክ ዲዛይነር ለአገር ውስጥ ደንበኛ የሚስማማ ብራንዲንግ ሲሰራ

ለብራንድ ዲዛይን WubSitesን ለምን ይመርጣሉ?

የአገር ውስጥ እውቀት፡ የኢትዮጵያን ገበያ ስለምናውቅ የድርጅትዎን ብራንድ ለአገር ውስጥ ደንበኞችዎ እንዲስማማ አድርገን እንሰራለን።

የፈጠራ ብቃት፡ ለሽልማት የታጩት ዲዛይነሮቻችን ለዓይን የሚማርክና ውጤት የሚያመጣ ብራንዲንግ መስራት ይወዳሉ።

ደንበኛን ያስቀደመ አሰራር፡ የድርጅትዎ ብራንድ ልዩ ማንነቱን እንዲያሳይ፣ የድርጅትዎን ራዕይና ዓላማ ለመረዳት ከእርስዎ ጋር በቅርበት እንሰራለን።

የተረጋገጠ ውጤት፡ በኢትዮጵያ ያሉ ብዙ ንግዶች በገበያ ላይ ጎልቶ የሚታይ፣ ጠንካራና በቀላሉ የሚታወቅ ብራንድ እንዲኖራቸው ረድተናል።

ድርጅትዎ የማይረሳ ብራንድ ይኑረው

ሎጎ ዲዛይን፡ የማይረሳ ሎጎ የድርጅትዎ ብራንድ መሰረት ነው። ለዓይን የሚማርክና ከድርጅትዎ እሴቶች ጋር የሚሄድ ሎጎ እንሰራልዎታለን።

የብራንድ መመሪያ ዝግጅት፡ የድርጅትዎ ብራንድ የሚታይባቸውን ነገሮች (ሎጎ፣ ቀለም፣ ፎንት) በሙሉ የሚዘረዝር መመሪያ እናዘጋጃለን፤ ብራንዱ በሁሉም ቦታ አንድ ዓይነት ሆኖ እንዲታይ።

ልዩ ግራፊክስ እና ስዕሎች፡ የድርጅትዎን ብራንድ የሚያሳምሩና የድርጅቱን ታሪክ ለደንበኞች የሚያስተላልፉ ልዩ ግራፊክሶችና ስዕሎች እንሰራለን።

የማስታወቂያ ቁሳቁሶች ዲዛይን፡ ከድርጅትዎ ብራንድ ጋር የሚሄዱና ውጤት የሚያመጡ፣ ዓይን የሚስቡ ብሮሸሮች፣ ፍላየሮችና ሌሎች የማስታወቂያ ቁሳቁሶች እንሰራለን።

ዌብሳይት ዲዛይን፡ ብዙ ጊዜ ደንበኛ ድርጅትዎን መጀመሪያ የሚያገኘው በዌብሳይትዎ ነው። ለዓይን የሚማርክ፣ ለመጠቀም ቀላልና የድርጅትዎን ማንነት የሚያሳይ ዌብሳይት እንሰራልዎታለን።

በአዲስ አበባ ለሚገኝ ድርጅት ተሰርቶ የተረከበ የብራንዲንግ ቁሳቁሶች ዲዛይን

ሁሌም ወቅታዊ የሚሆን ኮምፓኒ ፕሮፋይል

በብራንዲንግ ስራ 16 ዓመት አሳልፈናል፣ የኮምፓኒ ፕሮፋይል ዲዛይንም የዚሁ ስራ አካል ነው። ፕሮፋይል ቶሎ ያረጃል፡ አዲስ ምርት፣ አዲስ ቅርንጫፍ፣ አዲስ አድራሻ። ብዙ ጊዜ እያንዳንዱ ለውጥ አዲስ የዲዛይን ስራ ይጠይቃል።

ስለዚህ ፕሮፋይልዎን አንድ ጊዜ ዲዛይን አድርገን ወቅታዊ የሚያደርጉበትን መንገድ እንሰጥዎታለን። ለሙሉ አንድ ዓመት ይዘቱን በእኛ የማስተካከያ መሣሪያዎች ራስዎ ይቀይራሉ፤ ፕሮፋይል የሚያዘጋጀው መሣሪያችን ደግሞ ወደ ማተሚያ ቤት የሚልኩትን ለህትመት ዝግጁ ፋይል ያወጣልዎታል።

ሎጎ እና ብራንዲንግ ዲዛይን በአዲስ አበባ፡ ምን ያገኛሉ?

ብራንዲንግ ማለት ሰዎች አንድም ቃል ከማንበባቸው በፊት የሚያዩት ነው፡ ሎጎዎ፣ ቀለሞችዎ፣ ፎንቶችዎ እና የቁሳቁሶችዎ አቀማመጥ። እነዚህን እንደ አንድ ወጥ ስራ ዲዛይን እናደርጋለን፤ ታፔላዎ፣ ዌብሳይትዎ፣ የሶሻል ሚዲያ ገጾችዎና የህትመት ስራዎችዎ ሁሉ የአንድ ድርጅት መሆናቸው እንዲታወቅ።

ምን ምን ያካትታል

  • ሎጎ ዲዛይን ወይም እድሳት፡ ዋና ሎጎ፣ በፈካና በጠቆረ ጀርባ ላይ እንዲሁም በትንሽ መጠን የሚሆኑ ቅጂዎቹን ጨምሮ።
  • የብራንድ መመሪያ፡ ቀለሞችዎን፣ ፊደሎችዎንና የሎጎ አጠቃቀም ደንቦችን የሚወስን ሰነድ፤ ሰራተኞችዎና አታሚዎች ሁልጊዜ በአንድ ዓይነት መንገድ እንዲጠቀሙባቸው።
  • ስቴሽነሪ፡ ቢዝነስ ካርድ፣ መታወቂያ ካርድ እና የኮምፓኒ ፕሮፋይል።
  • የማስታወቂያ ቁሳቁሶች፡ ብሮሸር፣ ፍላየር እና የሶሻል ሚዲያ ፖስት ዲዛይን።
  • ለድርጅትዎ ብራንድ ተብለው የሚሳሉ ልዩ ግራፊክሶችና ስዕሎች።
  • ካስፈለገዎት በተመሳሳይ ስታይል ዌብሳይት ዲዛይን። ዌብሳይት ዲዛይን እና ግንባታ የሚለውን ይመልከቱ።

ስራው እንዴት ይሄዳል

  1. ነፃ የመጀመሪያ ምክክር። ስለ ንግድዎ፣ ስለ ደንበኞችዎ፣ ስለ ተወዳዳሪዎችዎ እና በሰዎች ላይ መፍጠር ስለሚፈልጉት ስሜት እንጠይቅዎታለን።
  2. ጥናት እና አቅጣጫ። ገበያዎን እናጠናለን፤ መሳል ከመጀመራችን በፊት አቅጣጫውን ከእርስዎ ጋር እንስማማለን።
  3. የሎጎ አማራጮች። የተለያዩ የሎጎ ሀሳቦችን እናቀርባለን፤ ከእያንዳንዱ ጀርባ ያለውን ምክንያትም እናስረዳለን።
  4. ማሻሻል። አንዱን አማራጭ ይመርጣሉ፤ በአስተያየትዎ መሰረት እናሻሽለዋለን።
  5. መመሪያ እና ርክክብ። የብራንድ መመሪያውን እንጽፋለን፤ ሌሎች ቁሳቁሶችዎንም በአዲሱ ስታይል እናዘጋጃለን።

ለማን ነው

ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እምነት የሚጣልባቸው ሆነው መታየት ለሚፈልጉ አዳዲስ ንግዶች። ሎጎአቸው ላረጀባቸው፣ ወይም በየሰነዱ በተለያየ መንገድ ለሚጠቀሙበት ነባር ድርጅቶች። አዲስ ዌብሳይት፣ አዲስ ማሸጊያ ወይም አዲስ ታፔላ ለሚያዘጋጁ ድርጅቶች።

ብራንድ ይበልጥ ውጤታማ የሚሆነው በሁሉም ቦታ በአንድ ዓይነት መንገድ ሲጠቀሙበት ነው። ለኢትዮጵያ አነስተኛና መካከለኛ ንግዶች የዲጂታል ማርኬቲንግ ዕቅድ መመሪያችን የድርጅትዎ ብራንድ ኦንላይን ላይ የት የት እንደሚታይ ያብራራል።

ከእርስዎ የምንፈልገው

  • የንግድ ስምዎና ስሎጋንዎ፣ በሚጠቀሙበት በእያንዳንዱ ቋንቋ ከትክክለኛ አጻጻፉ ጋር።
  • ምን እንደሚሰሩና ደንበኞችዎ እነማን እንደሆኑ የሚገልጽ አጭር መግለጫ።
  • የሚወዷቸውና የማይወዷቸው ብራንዶች ምሳሌዎች።
  • እድሳት ከሆነ፣ አሁን ያሉት የሎጎ ፋይሎችና ቁሳቁሶች።
  • በየደረጃው አስተያየት የሚሰጥ አንድ ውሳኔ ሰጪ።

ተደጋጋሚ ጥያቄዎች

በሎጎ እና በብራንዲንግ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

ሎጎ አንድ ምልክት ነው። ብራንዲንግ ደግሞ ሙሉው ስብስብ ነው፡ ሎጎ፣ ቀለሞች፣ ፎንቶች፣ የግራፊክ ስታይል እና የአጠቃቀም ደንቦች። ስራው ከሎጎ ይጀምራል፤ ብራንዲንጉ ደግሞ ሁሉንም አንድ ላይ አስተሳስሮ ይይዛል።

በኢትዮጵያ ሎጎ ማሰራት ስንት ያስከፍላል?

ዋጋው ሎጎ ብቻ ወይስ መመሪያና የህትመት ቁሳቁሶችን የያዘ ሙሉ ብራንዲንግ እንደሚፈልጉ ይወሰናል። ከነፃ ምክክሩ በኋላ ግልጽ ዋጋ አስቀድመን እንነግርዎታለን፤ የተደበቀ ክፍያ የለም። የዋጋ ግምት ይጠይቁ።

ያለንን ሎጎ ማደስ ትችላላችሁ?

አዎ። ነባር ደንበኞችዎ አሁንም እንዲያውቁዎት በጥንቃቄ እናድሰዋለን፤ የድሮው ሎጎ ለንግዱ የማይሆን ከሆነ ደግሞ እንደ አዲስ እንሰራዋለን።

አነስተኛ ንግድ የብራንድ መመሪያ ያስፈልገዋል?

መመሪያው አጭር ሊሆን ይችላል። አንድ ወይም ሁለት ገጽ እንኳን ቢሆን፣ አታሚም ይሁን ታፔላ ሰሪ ወይም ሶሻል ሚዲያዎን የሚያስተዳድር ሰው ዲዛይን በሰራልዎት ቁጥር ጊዜ ይቆጥባል።

ዌብሳይታችንንም ትሰራላችሁ?

አዎ። ዌብሳይት ዲዛይንና ግንባታም ስለምንሰራ ዌብሳይቱ ከድርጅትዎ ብራንድ ጋር አንድ ዓይነት ይሆናል። ገና እያሰቡበት ከሆነ በኢትዮጵያ ያለ ንግድ ዌብሳይት ያስፈልገዋል? የሚለውን ያንብቡ።

የኮምፓኒ ፕሮፋይሌን እንዴት ወቅታዊ አደርጋለሁ?

ይዘቱን በእኛ የማስተካከያ መሣሪያዎች ራስዎ ይቀይራሉ፤ ፕሮፋይል የሚያዘጋጀው መሣሪያችን ደግሞ ለማተሚያ ቤት የሚሆን ለህትመት ዝግጁ ፋይል ይሰጥዎታል። ይህ ለሙሉ አንድ ዓመት የዲዛይን ማሻሻያን ይሸፍናል፣ ስለዚህ አዲስ አድራሻ ወይም አዲስ ምርት አዲስ የዲዛይን ስራ አይጠይቅም።

ጥያቄዎን ይጻፉልን
ይህን ፎርም ይሙሉ፤ የዋጋ ግምት በፍጥነት እንልክልዎታለን።

Google Analytics የGoogle የዌብሳይት ትንተና አገልግሎት ነው። Google የሚሰበሰበውን መረጃ የዚህን ዌብሳይት አጠቃቀም ለመከታተል፣ ስለ እንቅስቃሴው ሪፖርት ለማዘጋጀት እና ለሌሎች የGoogle አገልግሎቶች ለማጋራት ይጠቀምበታል።

Google የተሰበሰበውን መረጃ በራሱ የማስታወቂያ ኔትወርክ ላይ የሚያሳያቸውን ማስታወቂያዎች ለእርስዎ እንዲስማሙ ለማድረግ ሊጠቀምበት ይችላል።

የሚሰበሰብ የግል መረጃ፡ ኩኪ እና የአጠቃቀም መረጃ። መረጃው የሚስተናገድበት ቦታ፡ አሜሪካ። የGoogleን የግላዊነት ፖሊሲ እዚህ ያገኛሉ።

Google Analytics የGoogle የዌብሳይት ትንተና አገልግሎት ነው። Google የሚሰበሰበውን መረጃ የዚህን ዌብሳይት አጠቃቀም ለመከታተል፣ ስለ እንቅስቃሴው ሪፖርት ለማዘጋጀት እና ለሌሎች የGoogle አገልግሎቶች ለማጋራት ይጠቀምበታል።

Google የተሰበሰበውን መረጃ በራሱ የማስታወቂያ ኔትወርክ ላይ የሚያሳያቸውን ማስታወቂያዎች ለእርስዎ እንዲስማሙ ለማድረግ ሊጠቀምበት ይችላል።

የሚሰበሰብ የግል መረጃ፡ ኩኪ እና የአጠቃቀም መረጃ። መረጃው የሚስተናገድበት ቦታ፡ አሜሪካ። የGoogleን የግላዊነት ፖሊሲ እዚህ ያገኛሉ።

የግላዊነት ፖሊሲ